ነዳጅና ፕሮፒላንት ኢንዱስትሪ

የነዳጅና ፕሮፒላንት ኢንዱስትሪ  ከተቋቋመባቸው ዓላማዎችና አንዱና ቀዳሚው ሀገራችን ባሏት በርካታ ታዳሽ ኃይሎች የተመሰረቱ የኢነርጂ ፕላንቶችና ፋሲሊቲዎችን በማልማት አካባቢያችንን ከሚበክሉ ጋዞች በማዳን እንቅስቃሴ የድርሻውን ለማበርከት ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ በጅምር የሚገኙና ሙሉ በሙሉ ጥቅም ላይ ያላዋሉትን የሀገራችን ፀጋዎች በተለይም የባዮማስና ባዮጋዝ ክምችቶችን በመጠቀም ከብክለት ነፃ የሆኑ የኢነርጂ ምጮችን ማምረት የኢንዱስትው ቀዳሚ ተግባር ሆኗል፡፡

ሀገራችን እያራመደችው ካለው የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ፖሊሲ አንፃርም ከዚህ ቴክኖሎጂ ግንባታና ከውጤቶቹም ተጠቃሚ እንድትሆን ከሚመለከታቸው አጋሮች ጋር ቀጣይነት ያለው የትብብር ስራ ይሰራል፡፡ በዚህም ከእህት ኢንዱስትዎች ጋር በመተባባር ለወታደራዊና ኮሜርሻል ስራዎች ፍጆታ የሚውሉ ልዩ ልዩ የኬሚካል ግብአቶችና ንጥረነገሮችን በተለያየ ዓይነትና መጠን እያቀረበ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እያደረገ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የሀገራችንን ሰላምና የህዝቦቻችን ደህንነት በዘላቂነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉና ጦርነት እንዳይከሰት በሩቁ ዲተረንስ የሚፈጥሩና ከተከሰተም በአጭሩ ለመቅጨትና በድል ለመወጣት የሚያስችለንን አቅም በመገንባት ደረጃ ኢንዱስትሪው ያራሱን ጉልህ አስተዋፅኦ ይወጣል፡፡

ተልዕኮ

ሀገራችን ባሏት በርካታ ታዳሽ ኃይሎች የተመሰረቱ የኢነርጂ ፕላንቶችና ፋሲሊቲዎችን በማልማት አካባቢያችንን ከሚበክሉ ጋዞች በማዳን እንቅስቃሴ የድርሻውን ማበርከት