ብኢኮ በኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት የተቋቋመና በኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማራ ልማታዊ ተቋም ነው፡፡
ብ.ኢ.ኮ በርካታ የወታደራዊና የሲቪል ምርቶች ማምረቻ ፋሲሊቲዎችን በመገንባት የሀገራችንን የኢንዱስትሪ ልማት በማፋጠን ላይ የሚገኝ ተቋም ነው
ብኢኮ በርካታ የማኑፋክቸሪንግና የሃይል ማመንጫ ፕላንቶችን ከዲዛይን እስከ ግንባታና የምርት ሙከራ ያሉ ስራዎችን ያከናውናል፡፡ ዋና ዋናዎቹ ፕሮጄክቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
በሀገር በቀሉ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮሬፖሬሽን (ሜቴክ) ሲገነባ የቆየው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ የሙከራ ጊዜውን አጠናቅቆ የስኳር ምርት ማምረት ጀመረ
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ባዘጋጀው የአርአያ ሴቶችና አርአያ ተቋማት የሽልማት እና ዕውቅና አሠጣጥ ስነ-ስርዓት ብኢኮ በሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት አርአያ ተቋም በመሆን ተሸልሟል፡፡
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አመራሮች ከአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከላት ከተውጣጡ ሶስት ሺህ ወጣቶች ጋር ተወያዩ፡፡