ሜጋ ፕሮጄክቶች

ብኢኮ በርካታ የማኑፋክቸሪንግና የሃይል ማመንጫ ፕላንቶችን ከዲዛይን እስከ ግንባታና የምርት ሙከራ ያሉ ስራዎችን ያከናውናል፡፡ ዋና ዋናዎቹ ፕሮጄክቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ የኤሌትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ

ብኢኮ የዲዛይን የምርት፣ የኢንስታሌሽንና ኢሬክሽን፣ የፓወር ሀውስ ዲዛይን ስራ፣ ስቲል ስትራክቸር፣ በኤሌክትሮ ሜካኒካል ሲስተም፣ የባላንስ ኦፍ ፕላንት አጠቃላይ ስራ እና የስዊች ያርድ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

የስኳር ፋብሪካ ግንባታ

ብኢኮ በሀገራችን በርካታ የስኳር ፋብሪካዎችን በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን እያንዳንዱ ፋብሪካ  በቀን 12,000 ቶን ሸንኮራ የሚፈጩና በዓመት እስከ 250,000 ቶን የሚደርስ ስኳር የማምረት አቅም ያላቸዉ ፋብሪካዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

የማደበሪያ ፋብሪካ ፕላንት

በኢሉአባቡራ ዞን ያዬ ወረዳ የሚገኘዉ የዩሪያ ማደበሪያ ፋብሪካ በዓመት 300,000 ሜትሪክ ቶን ዩሪያ የማምረት አቅም ያለዉ ሲሆን የዲዛይንና የፋብሪካ ግንባታ ስራዉም በብኢኮ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የእንፋሎት ሃይል ማመንጫ ፕላንት

ብኢኮ በርካታ የእንፋሎት ሃይል ማመንጫ ፕላንቶችን አየገነባ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም መካከል አንዱ የባዮማስ ኢነርጂ ፕላንት ሲሆን 137.5 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም አለዉ ፡፡

ሌሎች ፕሮጄክቶች

·         የፍሌክሲብል ማኑፋክቸሪንግ ወርክሾፕ ግንባታ

·         የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች

·         የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች

·         የደን ኢንዱስትሪ

·         አግሮ ፕሮሰሲንግ ፕላንት