የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን

ዳራ

ብኢኮ በኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት የተቋቋመና በኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማራ ልማታዊ ተቋም ነው፡፡

1.    ታሪካዊ ዳራ

ብኢኮ በሚንስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 183/2002 መሠረት በመንግስት የልማት ድርጅትነት ከመቋቋሙ በፊት በመከላከያ ሚኒስቴር ስር የመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በመባል የሚታወቅ ሲሆን በወቅቱ ወታደራዊ ምርቶችን፣ መጠገን፣ ማደስ፣ ማሻሻልና ዘመናዊ የማድረግ ስራዎችን ያከናውን ነበር፡፡ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብ.ኢ.ኮ በርካታ የወታደራዊና የሲቪል ምርቶች ማምረቻ ፋሲሊቲዎችን በመገንባት የሀገራችንን የኢንዱስትሪ ልማት በማፋጠን ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

2    ብኢኮ የተቋቋመበት አላማ

  •   የነጻ ገበያ ስርዓቱን ምክንያት በማድረግ የሚፈጠሩ ፍትሃዊ ያልሆኑ የገበያ ጉድለቶችን ለመሙላት
  •   በነፃ ገበያ ስርዓቱ የሚፈጠሩ መልካም አጋጣሚዎችንና መንግስት የሚመራውን የኢንዱስትሪ  ልማት ለማጠናከርና ለማፋጠን
  •   መንግስት የሚመራበትን ፖሊሲዎች በመከተል ኢኮኖሚውን ማሳደግ
  •   የህዝቡንና የግል ዘርፉን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ የማምረቻ ፋሲሊቲዎችን መገንባት

3    ልማታዊነት

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት የሚቀረፁ የልማት ስትራቴጂዎችና አቅጣጫዎችን በጥብቅ መከተል፡፡

4    በጋራ መስራት

በልማታዊ መስመር ውስጥ በጋራ የመስራት ባህል ጥልቅ ትኩረት የሚሰጠውና የምንከተለው አቅጣጫ ነው፡፡

   ብኢኮ የአሳታፊነትና የአጋርነት መርህን መከተል ለልማትና እድገት ቁልፍ እንደሆነ ያምናል፡፡ ከደንበኞች ከአጋሮችና አቅራቢዎች ጋርም በጋራ እንሰራለን፡፡

ብኢኮ የልማታዊ መንግስት ልማታዊ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ስራዎቹ ማህበራዊ ለዉጥን ማዕከል ያደረጉ ናቸዉ፡፡ሆኖም ከህዳሴ መስመሩ ግንባር ቀደም ተዋናይነቱና ከኢንዱስትሪ ልማት ንቅናቄዉ ጎን ለጎን ብኢኮ በማህበራዊ ኃላፊነት የበኩሉን ድጋፍ እየተወጣ ይገኛል፡፡በተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች፣ክሊኒኮች፣ድልድዮች፣የዉሃ ጉድጓዶችና የእንስሳት ህክምና መስጫ ማዕከላት ተገንብተዉ ህብረተሰቡ እንዲጠቀምባቸዉ ተደርጓል፡፡

ብኢኮ ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት የተሰኘ ሃገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከየክልሉ ህይወታቸዉን በጎዳና ላይ የሚገፉና ከ16 ሺህ በላይ ወጣቶችን ሰብስቦ በማሰልጠን የሙያ ባለቤት ሆነዉ በስራ ላይ እንዲሰማሩ እያደረገ ይገኛል ከዚህ በተጨማሪ ቤተሰቦቻቸዉ አነስተኛ ገቢ ያላቸዉ ተማሪዎችን እስከ ዪኒቨርሲቲ የሚዘልቅ ሙሉ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ እያደረገላቸዉ ይገኛል፡፡