የሎኮሞቲቭ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ

ሎኮሞቲቭ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ በ2003ዓ.ም በቢሾፍቱ አዉቶሞቲቭና ሎኮሞቲቭ ኢንዱስትሪ ተብሎ በብኢኮ ስር የተቋቋመ ኢንዱስትሪ ነዉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ዋና መ/ቤቱን አዲስ አበባ ከተማ ለገሃር ባቡር ጣቢያ ዉስጥ በማድረግና በድሬዳዋ ከተማ ተጨማሪ ፋብሪካዎችን በመክፈት ሀገራችን በባቡር ኢንዱስትሪዉ ዘርፍ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ባለቤት ለማድረግና በመንግስት የተነደፈዉን የአረንጓዴ ልማት ዕቅድ ለማሳካት ከአየር ብክለት ነፃ የሆኑ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ባቡሮችን በማምረት ስራ ላይ ተሰማርቷል፡፡ ኢንዱስትሪዉ በዋናነት የሀገራችንን የትራንስፖርት ችግር ከመቅረፍና የህብረተሰባችንን የትራንስፖርት ፍላጎት ከማርካት አኳያ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸዉ ባቡሮች በማምረት በቀጣይም ከሀገራችን አልፎ ለጎረቤት ሀገራት ኤክስፖርት በማድረግ የዉጭ ምንዛሬ ለማስገኘት አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ከምርቶቹም መካከል ቀላል የከተማ ባቡር፣ ሃገር አቋራጭ ባቡሮች፣የጭነት ማመላለሻ ፉርጎዎችንና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡

ተልዕኮ

*      የሃገራችን የምድር ባቡር ኢንጂነሪንግ የምርት ስራዎችን በላቀ ጥራት በማከናወን በተፈለገው ጊዜና ቦታ ማቅረብ

*      የምድር ባቡር ኢንዱስትሪ ምርቶቹ የሚመረቱባቸውን ፋብሪካዎች ዲዛይን፣ ተከላ፣ ገጠማ፣ ፍተሻና ርክክብ ስራዎች በማካሄድ የትራንስፖርቱን አገልግሎት ማሳደግ፡፡

*      የገቢ ምርቶችን በመተካት  አገራዊ አቅምን ማጎልበት የሚያስችል የቴክኖሎጂ ዓቅም ግንባታ መሰረቶችን ማጠናከር፡፡

*      በአለም አቀፍ የገበያ ውድድር መግባት፡፡

*      በምድር ባቡር ኢንጅነሪንግ ዘርፍ የዲዛይን፣የተከላና የሙከራ ዓቅሞችን መፍጠር የሚያስችል የአመራረትና የአተገባበር ቴክኖሎጂ ሰነድ በመንደፍ አገራዊ የባቡር መሰረተ ልማት ኢንጅነሪንግ ኔትዎርኪንግ ሲስተም መገንባት፡፡

*      የምድር ባቡር ኢንጅነሪንግ ልዩ ቴክኖሎጂ የሚሹ ማሽነሪዎችንና ስፔሻል ኢኪዩፕመንቶችን ማምረት፤ሃገራዊ አቅሞችን አሟጦ የመጠቀም ባህል በመገንባት ተመጋጋቢ የኢንጂነሪንግ መሳሪያዎች የግንባታ ዓቅም መፍጠር፡፡

ዋና ተግባር  (Core business)

*      የተለያየ ፍጥነት፤ ዓይነት እና ግልጋሎት ያላቸውን በኤሌክትሪክ እና በናፍጣ የሚሰሩ የሰው እና የዕቃ ማጓጓዣ  ባቡሮችን የባቡር አካላትን ዲዛይን ማድረግ ፤ ማምረት እንዲሁም ማስተላለፍ፡፡

*      የባቡር ማምረቻ ተቋም መትከል

*      የባቡር መስመር ዝርጋታ ስራ ማከናወን

*      የባቡር ኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ  ዕቃዎችን ማምረት እና የጥገና አገልግሎት መስጠት

*      የባቡር ዕውቀት ክህሎት ስልጠና መስጠት

 

ተጓዳኝ የስራ መስክ (Peripheral business)

*      የተለያዩ አይነት አውቶብሶችን ማምረት (Different type of buses, Cross country bus, Medium bus.)

*      የተለያዩ  የጀልባ ዓይነቶች ስራ (Boat)

*      የተለያዩ አይነት ተገጣጣሚ የብረት ኣካላት ዲዛይን ማድረግ፤ ማምረት እና መትከል(Steel structure)

*      ከላይ ከገለፅናቸው ስራዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው የስራ ላይና የመስክ ስልጠና መስጠት፡፡