የኳሊቲ ማኔጂመንት ማዕከል

አመሰራርትና ማንነት

የኳሊቲ ማኔጂመንት ማዕከል የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በአዋጅ መቋቋምን ተከትሎ  ሰኔ 2002 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ ስር ከተደራጁ የስራ ክፍሎች አንዱ ነው፡፡ ብኢኮ በተሰማራባቸው ስትራቴጂክ ቢዝነስ ዘርፎች ላይ አለም አቀፍ ተዋዳዳሪነቱን የሚያስጠብቁለት የጥራት ስታንዳርዶችን ከማረጋገጥ ባሻገር በሀገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችና የታላለቅ ፕሮጄክቶች ግንባታ ሂደት ሚያግዙ የጥራት መሰረተ-ልማቶች የማስፋፋት ተልዕኮ የተሰጠው ማዕከሉ የዘርፉ መሪ ተዋናይ ሆኖ እነዲዘልቅ አስችሎታል፡፡

ማዕከሉ በአሁኑ ሰዓት በስሩ ባደራጃቸው አራት የጥራት ማረጋገጫ ተቋማት ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም የካሊብሬሽንና ቴስቲንግ፣ የፕሮጄክቶች ጥራት ቁጥጥር፣ የስነ-ልክና ሰርቲፊኬሽን፣ የሳይንሳዊ አገልግሎት መስጫ መሳሪያዎች ምርትና ጥገና እና በዘርፉ ማሰልጠንና የማማከር አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡

ተልዕኮ

*      በብኢኮ እየተከናወኑ ያሉት ሜጋ ፕሮጄክቶች የጥራት ቁጥጥረና ክትትል ማድረግ

*      በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነና ደንበኞችን ማዕከል ያደረገ የካሊብሬሽንና ቴስቲንግ አገልግሎት መስጠት

*      በብኢኮና በሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ዘርፎች የሚመረቱ የሲቪልና ወታደራዊ ምርቶች እንዲሁም የሚሰጡ አገልግሎቶች ደረጃ ማውጣት፤ የጥራት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት እንዲያገኙ ማድረግ

*      በተቀመጡ መለኪያዎችና መስፈርቶች መሰረት የምርቶች የኢንስፔክሽን፣ የቬሪፊኬሽንና የኦዲት ስራ ማከናወን

*      የባዬሜዲካልና መሰል ሳይንትፊክ መገልገያ መሳሪያዎች ምርትና ጥገና