በማዕከሉ ውስጥ የተደራጁ ተቋማት

1.    የካሊብሬሽንና ቴስቲንግ ኢንስቲትዩት

የካሊብሬሽንና ቴስቲንግ ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ካሊብሬሽንና ቴስቲንግ አገልግሎት የሚሰጥ ብቸኛ ተቋም ነው፡፡ ኢንስቲትዩቱ በታጠቃቸው እጅግ የዘመኑ መሳሪያዎችና ባወጣቸው ተአማኒ የጥራት ደረጃዎች ዘመናዊ የፍተሻና ምርመራ አገልገሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፡፡ በዘርፉ የላቀ እውቀትና ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች የተደራጀው ኢንስቲትዩቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጠንና በዓይነት እየጨመረ መጥቷል፡፡

በዚህ ተቋም የሚሰጡ አገልግሎቶች ዘርፉን በበላይነት ከሚመሩ መንግስታዊ አካላት በቅርበት መስራት በመቻሉና በተለያየ ጊዜ ባገኛቸው አ/አቀፍ እውቅናዎች ምክንያት ተአማኒነታቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ደንበኞች የሚፈልጉትን አገልግሎት በጥራት በሚገልጉት ጊዜና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡላቸው ይተጋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ አገልግሎቶቹን የሚሰጥባቸው አራት ዘመናዊ ላብራቶሪዎችን አቅፏል፡፡ እነዚህም ጂኦሜትሪካል፣ ኤሌክቲሪካል፣ ተርማልና ሜካኒካል ላብራቶሪዎች ናቸው፡፡ ለብራቶሪዎቹ ከሚሰጧቸው አገልግሎቶች አንፃር በየመስካቸው ጥልቅ ፍተሻ ምርመር የሚደረግባቸው መሳሪያች ታጥቀዋል፡፡  

2.   የፕሮጄክቶች ጥራት ቁጥጥር ኢንስቲትዩት

የፕሮጄክቶች ጥራት ቁጥጥር ኢንስቲትዩት ብኢኮ በሚያከናውናቸው ሜጋ ፕሮጄክቶች የኳሊቲ ኮንትሮል፣ ኳሊቲ አሹራንስና ኢንስፔክሽን ተግባራትን ያከናውናል፡፡ በዚህም ፡

*      የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ

*      የኦሞ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ ፕሮጄክት

*      የበለስ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ ፕሮጄክት

*      የበለስ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ ፕሮጄክት

*      የያዮ ማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጄት

የጥራት ቁጥጥር ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጄክቶች ግንባታ ሂደት በዚህ ደረጃ እምነት የሚጣልበት አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም መገንባት ተችሏል፡፡

በፕሮጄክቱ ላይ በመሰጠት ላይ ያሉ አገልግሎቶች

*      የነን ዲስትራክቲቭ ቴስቲንግ (NDT) አገልግሎት

*      አልትራሶኒክ ቴስቲንግ

*      ራዲዮግራፊ ቴስቲንግ

*      ዌልዲንግ ኢንስፔክሽን

*      ስትራክቸራል ኢንስፔክሽን

*      ቦይለር ኢንስፔክሽን

*      የኤሌክትሪካል ዩኒቶች ኢንስፔክሽን

*      ኮንትሮል ዩኒትን

*      ትራንስፎርመር

*      የፕላንት ላብራላቶሪ ሲስተም ትግበራ

*      የፕላንት ላብራቶሪ መሳሪያዎች መረጣ

*      የማቴሪያል ቴስቲንግና የኢቫሉዌሽን ቴስቲንግ ውጤቶች

*      የሲብል ግንባታ ስራዎች ጥራት ቁጥጥር

*      የፕሮጄክቶች ሱፐርቪዥን ስራ

*      ከማምረቻ ፋብሪካዎች ጀምሮ እስከ ሳይት ያለው የኢኩዩፕመንቶች የምርት ሂደትና ጥራት መከታተል

*      የመጨረሻ የኢኩፕመንቶች ተከላ ኢንስፔክሽና ቴስቲንግ

*      በመጓጓዝ፣ በመጫንና በማውረድ ሊደርሱ የሚችሉ የኢኪዩፕመንት ጉዳቶችን መከላከል

*      ማሽነሪዎችና ኢከዩፕመንቶች በስታንዳርድ መሰረት መተከላቸውና መገጠማቸውን ማረጋገጥ

*       የሜካኒካል፣ ሃይድሮሊክና ኤሌክትካል ኮምፖኔንቶች ፍተሻ

*      የፕሮጄክቶች ርክክብ ክሊራንስ ማሰናዳትና መፈፀም

3.   የባዬሜዲካልና መሰል ሳይንትፊክ መገልገያ መሳሪያዎች ምርትና ጥገና ኢንስቲትዩት

*      የባዮሜዲካል ፕሪሲሽን ኢኩዩፕሜንት ጥገና

*      የሃይድሮኤሌክትሪክ ጄኔሬተሮች ጥገና

4.   የጥራት ደረጃዎችና ሰርቲፊኬሽን ኢንስቲትዩት

*      አገልግሎቶች

*      የብኢኮ ምርቶች ስታንዳርድ ማውጣት

*      በኢንዱስትሪያል ምርቶችና የምርት ጥራት ኢንስፔክሽንና ቨሪፊኬሽን

*      በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት የብኢኮ ምርቶች ሰርቲፊኬት እንዲያገኙ ማድረግ

*      ከኳሊቲ ማኔጂመንት ስታንዳርዶች (ISO 9001: 2008) አንፃር የጥራት ኦዲት ስራዎችን ማከናወን

*      በኳሊቲና ስታንዳርድ ላይ የስልጠና አገልግሎቶችን መስጠት