Ethiopia plastic Industry
Ethiopia plastic Industry (Version 1.0)

Version 1.0
Status: Approved
የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ምርት ማምረት ስራ ጀመረ፡፡ ላለፉት ሁለት ዓመት በላይ ምርት ማምረት አቁሞ የነበረው በብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የኢትዩጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ምርት ማምረት ጀመረ፡፡ ኢንዱስትሪ በአሁኑ ሰዓት በሙሉ አቅሙ የተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የፕላቲክ ምርቶችን ማምረት መጀመሩን የኢንዱስትሪው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጋሻው ይመር ተናግረዋል፡፡ ኢንዱስትሪው በማሽን መበላሸትና በጥሬ የምርት ግብዓት እጥረት ምክንያት የምርት ሂደቱ ቆሞ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የምርት ግብዓት የሚውሉ ከደቡብ ኮሪያ ግዢ የተፈፀመባቸው ጥሬ ዕቃዎች ኢንዱስትሪው ተረክቧል፡፡ ቀሪ የምርት ግብዓት ጥሬ ዕቃዎችም ወደ አገር ውስጥ እየገባ ሲሆን በሳምንታት ውስጥ ወደ ኢንዱስትሪው የማምረቻ ፋብሪካ መጋዘን እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡

Version | Date | Size | |
---|---|---|---|
1.0 | 10/29/19 1:54 PM | 930.4k |