ዝክረ መለስ አምስተኛ አመት መታሰቢያ

የታለቁ መሪ ጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ የ5ኛ አመት ዝክር በብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ማህበረሰብ በፓናል ውይይት በህሊና ፀሎትና በተለያዩ ዝግጅቶች ታስቦ ውሏል'በብኢኮ ዋና መስሪያ ቤት የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሲከበር በክብር እንግድነት የተገኙት የብኢኮ ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ዕለቱን አስመልክተውም እንደተናገሩት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ መለስ ዜናዊ የበለጸገች ኢትዮፒያን ለመገንባት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን በመቅረፅ በተለይም በኢንጅነሪንጉ ዘርፍ ስር ነቀል አስተዋጽኦ ያበረከቱ ነበሩ'ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በየደረጃው ያሉ አመራሮች የታላቁን መሪ አርዐያ በመከተል የሚጠበቅባቸውን መስራትና በርሳቸው የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል የበኩላቸውን እንደወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል'

በብኢኮ ዋና መስሪያ ቤት ከተዘጋጀው የዝክር ስነ-ስርዐት በተጨማሪ በኮርፖሬሽኑ ስር በሚገኙ ኢንደስትሪዎች&አገልግሎት ሰጪ ማዕከላት&የማምረቻ ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክት ሳይቶች የሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞች በችግኝ ተከላና እንክብካቤ&በፓናል ውይይት እንዲሁም በሻማ ማብራት ስነ-ስርዐትቶች ታላቁ መሪን አስበው ውሏል'

ከታላቁ መሪ ጠ/ሚኒስተር መለስ እፁብ ስራዎች(state of the art) አንዱ የሚባለው የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በሀገር መከላከያ ሚኒስተር ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውስጥ የነበሩትን ጥቂት የማምረቻ ፋብሪካዎችና የተፈጠሩ የቴክኖሎጂ አቅሞች ሀገሪቷ እያካሄደችው ለሚገኝ የኢንድስተሪ ልማት ስራ እርሾ ይሆን ዘንድ በአቶ መለስ ሀሳብ አፍላቂነት በመንግስት የልማት ድርጅትነት መቋቋሙ አየዘነጋም'