ብኢኮ ለሚያስገነባቸው የዋና መስሪያ ቤትና ሌሎች ሕንፃዎች ግንባታ ዲዛይን ላይ ውይይት ተደረገ፡፡

ብኢኮ ለሚያስገነባቸው የዋና መስሪያ ቤትና ሌሎች  ሕንፃዎች  ግንባታ ዲዛይን ላይ ውይይት ተደረገ፡፡

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ቁጥጥርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተዘጋጀው ሦስት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ሕንፃዎች የመጀመሪያ ዲዛይን ሥራ ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አመራሮችና የተለያዩ የሥራ ክፍል ሃላፊዎች ማብራሪያ ተደርጓል፡፡

ባለ16 ፎቅ ዋና መስሪያ ቤት፤የስልጠና ማዕከልና የድሕረ-ሽያጭና  አጠቃላይ የጋራጅ አገልግሎት የሚሰጡ ሕንፃዎችን ለማስገንባት በቀጣይነት የተያዙ የኮርፖሬሽኑ እቅዶች ናቸው፡፡

የዋና መስሪያ ቤቱ ሕንፃ ግንባታ 5ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ሲሆን ለልዩ ልዩ ስታፍ ቢሮዎች፤ሾው-ሩም፤የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎችና ሬስቶራንትና ካፌዎችን በውስጡ የያዘ ሲሆን  ሙዚየምም የተካተተበት ነው፡፡

በመካኒሳ አካባቢ ቀድሞ ባቱ ኮንስትራክሽን ተብሎ በሚጠራው የድርጅቱ  ቅጥር ግቢ የሚገነባው ዋና መስሪያ ቤቱ እስከ 180 መኪናዎች የመያዝ አቅም አለው፡፡

ሁለተኛው  የስልጠና ማዕከል ሕንፃ ግንባታ ለውስጥ ሰራተኞች አቅምን ለማጎለብት የተለያዩ ስልጠናዎች የሚሰጥበት ነው፡፡

በአንድ ጊዜ ከ3ሺ እስከ 4ሺህ ሰልጣኞችን መያዝ የሚያስችልና ለስልጠና አመቺ በሆነ መልኩ ዲዛይኑ ተዘጋጅቷል፡፡

ከዚህም ባሻገር  የተለያዩ የምርምርና ጥናት ስራዎች እንደሚከናወኑበት ታሳቢ በማድረግ  ነው ዲዛይኑ የተዘጋጀው፡፡ በዚህ የስልጠና ማዕከል ሕንፃ የአስተዳደር፤የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም ላብራቶሪና ወርክሾፖችን ታሳቢ ያደረገ ሕንፃ መሆኑን ከባለሙያዎች የቀረበው መረጃ ያመለክታል፡፡

እንዲሁም በሦስተኛነት ለውይይት የቀረበው የድህረ-ሽያጭና አጠቃላይ ጋራጅ አገልግሎት የሚውል የሕንፃ ዲዛይን ነው፡፡ የዚህ ሕንፃ ዲዛይን የዘመኑን ቴክኖሎጂ ታሳቢ ያደረገ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት የተካተተበት ነው፡፡

በዲዛይኖቹ ላይ የተቋሙ አመራሮች  ውይይት ያደረጉ ሲሆን በዚህ የዲዛይን ስራ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ቁጥጥርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ምስጋና ቀርቦለታል፡፡