ከወጣቶች ጋር ውይይት ተደረገ

ከወጣቶች ጋር ውይይት ተደረገ

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አመራሮች ከአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከላት ከተውጣጡ ሶስት ሺህ ወጣቶች ጋር ተወያዩ፡፡

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማትና የስራ ፈጠራ ዙሪያ የተደረገው ይህ ውይይት ወጣቶች አዳዲስ የፈጠራ ውጤቶችና የዲዛይን ፅንሰ-ሐሳቦች ይዘው በመምጣት ከብኢኮ ጋር መስራት እንደሚችሉ ዋና ዳይሬክተሩ ሜ/ጄነራል ክንፈ ዳኘው ገልፀዋል፡፡

      "ትውልድ እገነባለን" በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ ባህል ማዕከል አዳራሽ የተካሄደው ውይይት የመሩት ሜ/ጄነራል ክንፈ የሀገራችንን የኢንዱስትሪ ልማት ራዕይ ለማሳካት እንዲቻል ወጣቱ ትውልድ ራሱን በሳይንስና ቴክኖሎጂ እውቀት መገንባት እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡

      የብኢኮ ም/ዋና ዳይሬክተር ብ/ጄነራል ጠና ቁርንዴ በበኩላቸው ወጣቶች የነገ ሀገር ተረካቢዎች እንደመሆናቸው መጠን በኢንዱስትሪ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን የማድረግ ራዕይ መጋራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

በዕለቱ ወጣቶች እንዲብራራላቸው ላነሷቸው ጥያቄዎች በስራ ኃላፊዎች ገለፃ ተደርጓል፡፡ ከውይይቱ ባሻገር ዕለቱን በማስመልከት የተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም ታይተዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የተሳተፉ ወጣቶች የተፈጠረው መድረክ የፈጠራ ተነሳሽነታቸው እንዲጨምርላቸው ጠቅሰው ቀጣይነት እንዲኖረው ጠይቀዋል፡፡